እንኳን ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በደህና መጡ!
Welcome to Akaki Kality Sub-City — The Industrial Hub of Addis.
Welcome to Akaki Kality Sub-City — The Industrial Hub of Addis.
አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአዲስ አበባ የደቡብ በር በመሆን ያገለግላል። በኢንዱስትሪ መንደሮቹና በስትራቴጂካዊ መገኛነቱ ይታወቃል:: የአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ ከሚገኙ 11 ክፍለ ከተሞች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የአየር ንብረቱ እና መልክአ ምድራዊ አቀማመጡም ከአዲስ አበባ መሀል ከተማ በተለየ ዝቅተኛ ስፍራ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ለኢንዱስትሪ ግንባታ ምቹ የሆነ ሜዳማ መሬት እና ሞቃታማ የአየር ንብረት ያለው ክፍለከተማ ነው።
ሌላው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለከተማ የሚታወቀው፤ በታሪካዊነቱ፣ በኢንዱስትሪ ቀጠናነቱና ለከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ባለው ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ ነው። ይህ ክፍለ ከተማ የከተማዋ "የኢንዱስትሪ ሳንባ" እና የንግድ መስመር መገጣጠሚያ በመሆኑ ከመደበኛ የአስተዳደር ወሰን ባለፈ ሀገራዊ ፋይዳው የጎላ ነው።
አካባቢያዊ መለያውም የከተማና የገጠር ድባብን አጣምሮ የያዘ፣ ለኢንቨስትመንት ምቹና የወደፊት ተስፋው ብሩህ የሆነ የልማት ክፍለ ከተማ ነው። ክፍለ ከተማው 11810 ሄክታር የሚሸፍን የቆዳ ስፋት አለው። ይህ ስፋቱ ለታላላቅ ፋብሪካዎች፣ ለትራንስፖርት ተርሚናሎችና ለሰፋፊ የመኖሪያ መንደር ልማቶች ምቹ አድርጎታል።
አቃቂ ቃሊቲ በሰሜን እና በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ የሚያዋስኑት ክፍለ ከተሞች፤ የካ ክፍለ ከተማ በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ የሚያዋስነው ሲሆን፤ ቦሌ ክፍለ ከተማ በሰሜን እና በሰሜን ምስራቅ አቅጣጫ ይዋሰኑታል። ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ደግሞ በሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ይዋሰነዋል።